♦️ሦስት ነገሮችን ጠብቅ!
# ሀገር
# እናት
# ዓይን
♦️ለሦስት ነገሮች ተዘጋጅ!
# ለኃላፊነት
# ለእውቀት
# ለትዳር
♦️ሦስት ነገሮችን አክብር!
# ቃልኪዳን
#ጓደኛ
# ትዳር
♦️ሦስት ነገሮችን ተቆጣጠር!
# ምላስህን
#ቁጣህን
# ስሜትህን
♦️ሦስት ነገሮችን አድንቅ!
# ውበት
# ሕይወት
#ተፈጥሮን
♦️ሦስት ነገር ጥላ!
# ሀሜት
#ቅናት
# ተንኮል
♦️ሦስት ነገሮች ያስፈልጉሃል!
# እምነት
# ተስፋ
# ፍቅር
📍(1)ብቸኛ ሆኖ ብቸኝነት ማጣጣም በአስመሳይ ስዎች ከመከበብ ይሻላል
📍(2)አንድን ነገር ማድረግም አለማድረግም ከፈለክ ምክነያት አይጥፈም
📍(3)ምርጡ ዶክተር ፈጣሪ መድሀኒት ደግሞ ፀሎት
📍(4)ለስው ልትስጠው የምትችለው ትልቁ ስጦታ ጊዜህን ነው
📍(5)‹‹ውድቀትን አትፍራው፡፡ ውድቀትን ለመደበቅ ጉልበትህን አታባክን፡፡ ከውድቀትህ ተማርና ወደቀጣዩ ፈተና ቀጥል፡፡ ውድቀት መጥፎ ነገር አይደለም፡፡ ካልወደክ ወደፊት አትራመድም፡፡
📍(6)‹‹እያንዳንዱ ነገር ውበት አለው፤ ማንኛውም ሰው ግን አያስተውለውም፡፡
‹‹ፈተናዎች ህይወትን ተወዳጅ የሚያደርጉት ሲሆን ህይወትን ትርጉም ያለው የሚያደርጋት ፈተናዎቹን መቋቋም ነው፡፡››
📍(7)‹‹ደስታ ተዘጋጅቶ የተቀመጠ ነገር አይደለም፣ ከራስህ ተግባራት የሚመጣ እንጂ፡፡››
📍(8)‹ጠንካራ መሆን ማለት በራስ ማንነት መደስት ማለት ነው፤ ከነ - ድክመቶችክ!›› -
📍(9)‹‹የምትፈልገውን ነገር ተከትለህ ካልሄድክ በስተቀር አታገኘውም፣ እስካልጠየክ ድረስ ምላሹ ምንግዜም አይደለም ነው፡፡ ወደፊት እስካልተራመድክ ድረስ ምንግዜም አንድ ቦታ ላይ ነህ፡፡››
📍(10)ከሰው ቤት እንጀራ ከፍትፍት መረቁ
የእናት ይሻላል ዘንጋዳው ደረቁ
- የሚታኮስ ወታደር ነህ። ድክመትህ ሲጋለጥ ተመተህትወድቃለህ። ለመፈቀር ብለህ አታስመስል። አስመስለህ በቀረብከው ተወደህ ከምትጠላ ራስህን ሆነህ ብትኖር።የሆንከውን የምትወድልህ አታጣም። በዚህ ጊዜ ፍቅር ውበት ሆኖያስደስትሀል። ሁሌ እራስህን ሁን!! ...
- ከእያንዳንዱ ብረሀን ጀርባ ጨለማ እንዳለ አስተውል፡፡ ያለህበት ብርሀን ዘላቂ እንዲሆንልህ ዘንድ መልካም ነገሮችን ብቻ አድርግ፡፡ ክፋት ካከልክበት ከጨለማው ስር ትወድቃለህና፡፡
"🦋 ስቀልድ ነበር " ከምትለዋ ቃል ጀርባ
ትንሽ እውነታ አለች
🦋" አረ ችግር የለውም " ከምትለዋ ቃል ጀርባ
ትንሽ ስሜት/ህመም አለች
🦋" ምንም አልፈልግም " ከምትለዋ ቃል ጀርባ
ትንሽ ፍላጎት አለች…
🦋"መሄዴ ነው"ከምትለዋ ቃል ጀርባ የመቅረት
ፍላጎት አለች
🦋. . . . . . . . .ነገር ግን ከዝምታ ጀርባ ብዙ ብዙ
ቃላቶች አሉና ቃላቶችን ብቻ ሳይሆን ስሜቶችንም
ለመረዳት ሞክሩ!!. . . .
- ጓደኝነት ዋጋ የሚኖረው ስትውደው ብቻ የሚውድህ ሳይሆን ፡ = ስትደስት ብቻ አብሮህ የሚሆን ስትጠላውም ከጥላቻ ስሜት አልፎ ይቅር🙏 የሚልህ ሲከፈህም😟 አብሮህ የሚሆን ነው፡ 😒ግን ምን ያደርጋል ሁሉም የራሱን ስሜት ብቻ የዳምጣል 😂ስትደስት አብሮህ ይሆናል ሲከፋህ ትቶህ ላሽ ይላል... ግን ምንም ቢሆን ሁልጊዜም አንት ለስዎች 👨👨👧👦መልካም ሁን 😉ፈገግታህን አትንፈጋቸው፡፡ ምናልባት አምላክ ከነሱ የተሻለ ስላንተ የሚጨነቅና የሚያስብልህን 👍ጓደኛ👫 ይስጥህ ይሆናል😍፡
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
❀ህሊና በሰው የሚገኝ የፈጣሪ ምትክ ነው✿
❀ዝም ማለት ሁልግዜ እሺ ማለት አይደለም አንዳንዴ ለማይገባው ሰው ማብራራት ሰልችቶኛል ማለት ነው❀
❀እንደ ጀግና ኑር ከጀግናም ጋር ታገል እድል ብቅ ትል ይሆናል❀
❀ጨለማን ያላየ መብራ አያደንቅም መውደቅን ያላየ መነሳት አያውቅም❀
❀ውበት የአምላክ ስጦታ ናት!❀
"በህይወትህ ትእግስተኛ መሆን ከቻልክ የምትፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ ግዜያቸውን እየጠበቁ ወዳንተ ይመጣሉ፡፡
በፍቅር አለም ውስጥም ትልቁን ዋጋ ሚያስከፍለው ትእግስት ነው፡፡ መታገስ ይከብዳል፡፡ ያ' ግዜ ሲያልፍ ግን ምንፈልገውን እናገኛለን፡፡መራራውን ግዜ አልፈህ ጣፋጩን ፍሬ ትበላ ዘንድ ታጋሽ ሁን፡፡ ትእግስተኞች ከ ጉልበተኞች ይበልጣሉ፡፡"
💝🕛ፍቅር በወረቀት ላይ አይጻፍም፣ ወረቀት ላይ የተጻፈው ሊሰረዝ ይችላል፡፡ እንዲሁም ድንጋይ ላይ አይቀረጽም ምክንያቱም ድንጋይ ላይ የተቀረጸ ሁሉ ሊሰበር ይችላል፡፡ ነገር ግን በልብ ላይ ታትሞ እና ለዘላለም ጸንቶ ሊቀር ይችላል፡፡
…✍️በህይወቴ ከተማርኩት ነገር ውስጥ አንደኛው ለሰዎች መልካም ነገር ብታደርግ ለመልካምነትህ ከሰዎች ዘንድ ምላሽ መጠበቅ ሊጎዳ እንደሚችል ነው።
❖✿አንዳንዱ መልካም ስታደርግ ሞኝ እንደሆንክ ሊቆጥርህ ይችላል።
❖✿አንዳንዱ ደግሞ ከእሱ የሆነ ነገር ፈልገህ የምታደርግለት ይመስለዋል።
፠=ሌላኛው ደግሞ ከምስጋና ይልቅ ጠላትህ ሊሆን ይችላል።
=፠እናም እልሀለሁ ለመልካምነትህ
ከሰዎች ምላሽን አትጠብቅ!
፠=ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ ምላሹ
ምንም ይሁን ምን መልካምነት አብሮህ ይሁን! ፈጣሪህ ይከፍልሀልና!
🌟ለሁሉም ነገር መጠን አብጅ።
ከፍታህን በቁመትህ ልክ አድርግ። ከራስህ በላይ የሆነ ከፈታ መፈጥፈጥ ሊያስከትል አንደሚችል አስብ።
ውድቀትህም ከጫማህ በታች እንዳይሆን አድርግ።
ከውድቀት በኋላ አልነሳም ብሎ ማሰብ ከጫማ በታች መቀበር እንደሆነ ገምት።
ወድቆ መነሳትን ከቅርጫት ኳስ ተማር። ወድቆ የሚነጥር ማንነት ይኑርህ። ነጥሮም ቀለበቷ ውስጥ ነጥብ የሚያስቆጥር ህይወት ይኑርህ።
ወደ ከፍታ የወጣ ሁሉ ስኬት እንዳልሆነ እወቅ። ውድቀት መቀበር እንደሆነ ሁሉ መነሳትም መንሳፈፍ እንዳይሆንብህ ጥንቃቄ አድርግ።
በምትወድቅበት ጊዜ ላለመቀበር፣ በምትነሳበትም ጊዜ ላለመንሳፈፍ ይሆን።
"ህይወት የራሱ ቅኝት አለው ። በህይወት ውስጥ የሚገጥሙ ማንኛውም ነገሮች ሲገጥሙ ከተነጫነጭን ቅኝቱ ይበልጥ ይጠብቃል። ነገር ግን ጥሩ ነገሮች ማየት ከቻልን ጥሩ ነገሮች ይጨመራሉ። በማንኛውም ነገር ውስጥ የሚመሰገንበትን ነገር ማየትና ህይወትን ወደ በረከት መለወጥ ይቻላል ።"
➊ ምን ጊዜም ለስዎች አሰፈላጊያቸው እንጂ ፈላጊያቸው አትሁን! ከቻልክ ለችግራቸው ደራሽ ሁን ለችግርህ ውይንም ለጥቅምህ ግን አትፈልጋቸው፡፡
➋ ስው ወሬ አያጣም/ ደግ ፡ብትሆንለት~ተርፎት ነው :
ብትቀርበው~ልምምጥ ነው ፡ዝም ብትል~ነገርኛ ነው ፡ ብትረሳው ~ትቢተኛ ነው እያለ ያወራብሀለ፡፡
➌ ቅጠረን ይሉኛል ፡ስዎች ሳይገባችው ትርፍ ቦታ የለም ብለሽ ንገሪያቸው ተንስራፍተሸበት በ አእምሮዬ ጓዳ አንቺን ዬት አድርጌ ልቀበል እንግዳ
➍ ሚስት ማግባት ትዝ የሚልህ ልጆችን ስታይ ከሆነ ሚስትህን የምትፈልጋት ለርቢ ነው ማለት ነው
➎ በአንድ ምክንያት የሚወድክ ስው ፡ በሌላ ምክንያት ይርቅካል ለምን እንደሚውድክ ማያቅ ግን ሁሌም ይወድሀል
➏ ከሠዎች ጋር ሮጠህ ያልደረስክበት ነገር ካለ ወደ ተነሣህበት ተመለስ!
ከፈጣሪ ጋር መሮጥ ጀምር የኔ ካስብክበት ሣይሆን ያስበልክ ቦታ ትደርሣለክ!!!
➐>በመራራቅ ውስጥ በጣም የሚያስፈራው ነገር ይናፍቁህ ወይ ይርሱህ አለማወቅህ ነው
➑ ችክ አትበልበተት
❤️ስትውደው😏 ከጠላክ : ስትነገረው ካልስማህ ፡ ስስጠው ፊትህን ፡ ከስጠህ ጅርባውን ፍፁም ካልተረዳው አስተሳስብህን ችክ አትበልበት አትለማመጠው ወዳጅ አይሆንህም በግድ ያስጠጋኸው
💞ፍቅር በተላላቆች እይታ💕
🌿❣️"ፍቅር ያለ እምነት ነፋስ ላይ እንደተቀመጠ
ሻማ ነው!" (ቶማስ ሚድልተን)
🌿❣️ "በፍቅር ለሚወድቁ ሰዎች የመሬት ስበት
በፍፁም ተጠያቂ አይደለም!" (አልበርት እንስታየን
🌿❣️"ፍቅር በተፈጥሮ የሚታደሉት ሲሆን ፣ የተሳካ
የሚሆነው በቅንነት ጠበቅ አርገው ሲገፉበት ነው
(አሪስቶትል)
🌿❣️" ፍቅር በእልህ ፣ በችኮላ ፣ በንትርክና በግዴታ
የሚያሸንፉት ቀላል ስሜት አይደለም !!!"
(አጋታ ክርስቲ)
🌿❣️"በፍቅር ውስጥ ያለው ድል ማሸነፍ ነው!!"
(ናፖዎሊዩን ቦናፓርት)
🌿❣️"ፍቅር የቡድን ስራ አይደለም!!!"(አሰፉ ጉያ)
🌿❣️"ፍቅርን ፍቅር የሚያሰኛት አብረው ያሳለፉት
ረዥም ጊዜ አይደለም ፣ ፍቅር የምንላት የአንድ
ደቂቃ ጉዳይ ቢሆንም ጣዕሟ ለዘላለም የማይረሳ
ከሆነ ፣ እስዋን ነው ፍቅር የምንላት !!!!!"
(ደራሲ በዓሉ ግርማ)
🌿❣️"ፍቅር ገንዘብ ማስቀመጫ ኪስ የሌለው
ራቁቱን የሆነ ልጅ ነው!! "(አቪድ)
🌿❣️"ፍቅር ጥልቅ ቦታ እንጂ በከንፈር ውስጥ
ብቻ ሊኖር አይችልም!!!" (ቴኔሰን)
🌿❣️"ፍቅር ውሻ እንኳን በግጥም እንዲጮኽ
የሚያረግ ኃይል አለው!!" (ፍራንሲስ ቦም)
ከልብስህ ይልቅ ልብህ እንዳይቆሽሽ ጥንቃቄ አድርግ
.
ልብስህን ከአቧራ እና ቆሻሻ እንደምትጠብቅ ሁሉ ልብህንም ከተንኮል፣ ከክፋት፣ ከትዕቢት፣ ከሃሜት፣ ከቅናት እና ከምቀኝነት ጠብቃት
.
ልክ እንደ ልብስ ልብም ሲቆሽሽ ጠረን ያመጣል ::
📝❤️✔️እውነተኛ ፍቅር) ✏️❤️✡️🔯
📍1☂️እውነተኛ ፍቅር ፈጣሪ ከገነት በታች ለሰው ልጆች የሰጠው ስጦታ ነው፡፡
📍2☂️ለፍቅር ሁነኛ ማረጋገጫ እምነት ነው፡፡
📍3☂️ማንም ሰው አይናችን ውስጥ ሊገባ ይችላል፤ ነገር ግን ልባችን ውስጥ ዘልቆ የሚገባው አንድ ልዩ ሰው ነው፡፡
📍4☂️ራስህን እንድትሆን ለማይፈቅድልህ የፍቅር ወዳጅነት ራስን አሳልፈህ አትስጥ፡፡
📍5☂️በሌሎች የመፈቀርን ሀሰብ ከመውደድ በፊት፤ መጀመሪያ ራስን መውደድን ተማር፡፡
📍6☂️በማይረባ ድንጋይ ጊዚያቸውን እንዳባከኑ ሲገባቸው በእጃቸው የነበረው እንቁ እንደነበር ይገነዘባሉ፡፡
📍7☂️አንድን ሰው ለመልኩ ብቻ አናፈቅረውም፣ ለአለባበሱ ወይም ለምርጥ መኪናውም ልናፈቅረው አይገባም፤ የምናፈቅረው እኛ ብቻ ልንሰማው የምንችለውን ዜማ ስለሚያቀነቅኑ ነው፡፡
📍8☂️ፍቅር ማለት ወሲብ አይደለም ፣ ወይም ጥሩ ምሽቶችን በጋራ ማሳለፍም አይደለም ፣ ወይም ተቃቅፎ መታየም ሳይሆን ማንም ሊያስደስታችሁ በማይችልበት መንገድ ደስታን ሊፈጥርላችሁ ከሚችል ሰው ጋር አብሮ መሆን ነው፡፡
📍9☂️ፍቅር እውር አይደለም ፣ ሌሎች በቀላሉ ሊያዩትን ያልቻሉትን ነገር እንዲያዩ የሚያስችል እንጂ!
👍10☂️ላረጋግጥልሽ የምፈልገው ነገር ቢኖር፣ ምን ያህል እንደምናፍቅሽና አንቺ ካጠገቤ ርቀሽ አለም ምን ያህል ባዶ እንደሆነችብኝ ነው፡፡
✍️" እንቁራሪቶች ከበሬ የበለጠ ሊጮሁ ይችላሉ ። ነገር ግን የእርሻ መሬት ላይ ማረሻ መሳብ ወይም የወይን መጥመቂያ መሳሪያ ማሽከርከር አይችሉም። ቆዳቸውም ጫማ ለመስራት አያገለግልም።"
#የሠው_ልጅ_ሊሆን_የሚችለው_ራሡን_ብቻ_ነው።
✍️✍️#አስተዋይ
👉ያለበት ጊዜ የገባው ሠው ነው
👉መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል
#ተናጋሪ_ሁሉ_አዋቂ_አይደለም፤
#ዝም_ያለ_ሁሉም_ሞኝ_አይደለ
ከቁጥጥርዎ ውጪ ለሆኑ ነገሮች መጨነቅና መረበሽ #ያቁሙ❌
~የልባችሁን ሃሳብ ተከተሉ ነገር ግን አእምሮአችሁን መጠቀም አትርሱ
~ቃላትን እንጂ ድምፃችሁን አታጩሁ
#አበባ_በዝናብ_እንጂ_በመብረቅ_አያድግምና✍️✍️❗️❗️❗️
ሣቅ ደሥታን አይገልፅም ©©
°°°°°••••• •••••• •••••••••°°°°°°
ብሦቴን በሆዴ ችግሬን ባንጀቴ
ጥርሤ ፈገግ ቢል ፀዳል ቢለብሥ ፊቴ
.
ማን አየልኝና የውሥጥ እርዛቴን
ከኔ ውጭ ሌላ ማን ያውቃል ጉዳቴን?
.
ውሥጤን ሣትረዱ ምነው መፍረዳችሁ
ደሥ አለህ አትበሉኝ ጥርሤን እያያችሁ።
...........እሥኪ እኔም ልጠይቅ?
እምባችን ለሀዘን ሣቅ ብቻ ለደሥታ
እንድንገልፅበት ሆነ እንዴ ግዴታ?
.
.............አንዳንዴም
እምባኮ ይፈሣል ምንም ሣይከፉ
ደሥታ ጣራ ሢደርሥ ድል ሢጎናፀፉ።
.....ያውም የድል እምባ ደሥ የሚል ሢያለቅሡ
....ውጣ ውረድ አልፈው ሥኬት ላይ ሢደርሡ
.
................ደሞም
በእሣት እያረረ ማሽላ ይሥቃል
የያዘውን ሚሥጥር የሆዱን ማን ያውቃል???
.
.......... እኔም እንደዚህ ነኝ
በጥርሤ እሥቃለሁ ምን ሆዴ ቢቆጭም
ማልቀሤን ለሚሹ እምባየን አልረጭም።።።
No comments:
Post a Comment